ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
ኦክቶ 25 2025
አጠቃላይ

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ እና ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በጋራ ለመስራት በሚችሉባቸው ዘርፎች ላይ ዉይይት አደረጉ።

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የግብርና ዘርፍ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፈለቀ ታደሰ የተመራ ቡድን እና ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል ዩሱፍ እና ከሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋር በግብርና ዘርፍ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አካሂደዋል፡፡ ሁለቱ ተቋማት የዩኒቨርሲቲውን የተማረ የሰው ኃብትና የምርምር ውጤቶችን ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሀብት ጋር አቀናጅቶ ለሀገር የሚጠቅም ስራ ለመስራት መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡ […]

photo 2025 10 25 10 04 22
photo 2025 10 25 10 04 22

በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የግብርና ዘርፍ ም/ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፈለቀ ታደሰ የተመራ ቡድን እና ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል ዩሱፍ እና ከሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋር በግብርና ዘርፍ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት አካሂደዋል፡፡

ሁለቱ ተቋማት የዩኒቨርሲቲውን የተማረ የሰው ኃብትና የምርምር ውጤቶችን ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሀብት ጋር አቀናጅቶ ለሀገር የሚጠቅም ስራ ለመስራት መስማማታቸውን ገልጸዋል፡፡

በጋራ የሚሰሩ ጉዳዮችን በመለየት  በቅርቡ ስምምነት በመፈራረም ወደ ስራ እንደሚገቡም ይፋ አድርገዋል።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የስራ ኃላፊዎች በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በምርምርና ኢንተርፕራይዝ ልማት፣ በግብርና ዘርፍ የተከናወነው ስራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ሚድሮክ ለሀገር- ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ