ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
ኦክቶ 24 2025
አጠቃላይ

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕና ሌሴቶ በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ዉይይት አደረጉ።

በኢትዮጵያ የሌሴቶ አምባሳደር እንትጺዋ ካስቲሊያ ሴኬቴ ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አመራሮች ጋር አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ዉይይት አድርገዋል። አምባሳደሯ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ በተለይም ከስራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀዋል።ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሀገር ውስጥ ያለውን አቅም ወደ ሌሴቶ በማምጣት በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ እንዲሰማራም አምባሳደሯ ጥሪ አቅርበዋል። የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ […]

0Y9A5039 min
0Y9A5039 min

በኢትዮጵያ የሌሴቶ አምባሳደር እንትጺዋ ካስቲሊያ ሴኬቴ ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አመራሮች ጋር አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ዉይይት አድርገዋል።

አምባሳደሯ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ በተለይም ከስራ እድል ፈጠራ ጋር በተያያዘ እየሰራ ያለውን ስራ አድንቀዋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በሀገር ውስጥ ያለውን አቅም ወደ ሌሴቶ በማምጣት በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ እንዲሰማራም አምባሳደሯ ጥሪ አቅርበዋል።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ቺፍ ኦፕሬሽን ኦፊሰር አቶ አበበ ተክሉም ግሩፑ ከሌሴቶ ጋር በተለያዩ ዘርፎች ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

በደቡባዊ አፍሪካ የምትገኘው ሌሴቶ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎች እንዳሏት አምባሳደሯ ገልጸዋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና፣ በማዕድን፣ በንግድና አገልግሎት፣ በሆስፒታልቲ እንዲሁም በኮንስትራክሽንና ሪል እስቴት ዘርፎች የተደራጁ 45 ኩባንያዎችን ያቀፈና 79 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል መፈጠር የቻለ ተቋም ነው ።

ሚድሮክ ለሀገር- ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕና ሌሴቶ በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ዉይይት አደረጉ። | ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ