ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
ኦክቶ 29 2025
አጠቃላይ

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አካል የሆነው ዴይላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂስ ሀላ/የተ/የግል ማህበር በአፍሪካ ደረጃ የካይዘን ሥርአትን ተግብረው ለውጥ ከማምጣት አንፃር የተሻለ ውጤት ካስመዘገቡ ድርጅቶች ጋር በመወዳደር በአንደኛ ደረጃ ተሸላሚ መሆን ችሏል።

የድርጅቱ መሸለም እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ግሩፕ የሚያኮራ ሲሆን ይህንን ውጤት ወደ ሌሎች ድርጅቶች ለማጋባት ጥሩ መነሻ እንደሚሆን ይታመናል። በሌላ በኩል ድርጅቱ ከአምስት ዓመታት በፊት በከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ የነበረ ሲሆን ባለፉት አራት ዓመታት ግን አትራፊና በተከታታይም በወርቅ ደረጃ ከፍተኛ ግብር ከፋይ በመሆን እውቅና ያገኘ ድርጅት መሆን ችሏል። ከዚህ በተጨማሪ በግሩፑ ስር እንደሚተዳደር አንድ ድርጅት የተለያዩ […]

d335204e 2f70 4451 9aa9 6d8222233d62
d335204e 2f70 4451 9aa9 6d8222233d62

የድርጅቱ መሸለም እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ግሩፕ የሚያኮራ ሲሆን ይህንን ውጤት ወደ ሌሎች ድርጅቶች ለማጋባት ጥሩ መነሻ እንደሚሆን ይታመናል።

በሌላ በኩል ድርጅቱ ከአምስት ዓመታት በፊት በከፍተኛ ኪሳራ ውስጥ የነበረ ሲሆን ባለፉት አራት ዓመታት ግን አትራፊና በተከታታይም በወርቅ ደረጃ ከፍተኛ ግብር ከፋይ በመሆን እውቅና ያገኘ ድርጅት መሆን ችሏል።

ከዚህ በተጨማሪ በግሩፑ ስር እንደሚተዳደር አንድ ድርጅት የተለያዩ የአሠራር ሥርዓቶችን ከመተግበር አንፃር:- የጥራት ሥራ አመራር ሥርዓት፣ የሥራ ላይ ጤናና ደህንነት ሥርዓት፣ የአካባቢ ጥበቃ ሥራ አመራር ሥርዓት እና የኢንተግሬትድ ማኔጅመንት ሥርዓትን መተግበርም ችሏል።

እንደ ግሩፕ እንዲህ አይነት በአህጉር አቀፍና በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚደረጉ የልህቀት ውድድሮች ላይ ቀዳሚ በመሆን ለሌሎች አርአያ ለመሆን በትጋት የሚሠራ ይሆናል።