ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
ኤፕሪ 7 2026
አጠቃላይ

ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ እና ‘BeU Delivery’ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ልዩ የአጋርነት (Exclusive Partnership) ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ንጉሡ ሰለሞን እና የ’BeU Delivery’ የማርኬቲንግና ቢዝነስ ዲቨሎፕመንት ማናጀር አቶ ብሩክ ገነነ ተፈራርመዋል። ይህ ስምምነት ‘BeU Delivery’ የሞሐ ምርቶችን በልዩ ሁኔታ እንዲሸጥ እና እንዲያስተዋውቅ የሚያስችል ሲሆን፤ ደንበኞች በተመረጡ ሬስቶራንቶች በ’BeU Delivery’ በኩል ምግብ በሚያዙበት ወቅት ፔፕሲን በነፃ እንዲያገኙ ዕድል ይሰጣል። ሁለቱ ተቋማት በጋራ በመሥራት የኢትዮጵያን የአገልግሎት ዘርፍ […]

701A2301
701A2301

ስምምነቱን የሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ ንጉሡ ሰለሞን እና የ’BeU Delivery’ የማርኬቲንግና ቢዝነስ ዲቨሎፕመንት ማናጀር አቶ ብሩክ ገነነ ተፈራርመዋል።

ይህ ስምምነት ‘BeU Delivery’ የሞሐ ምርቶችን በልዩ ሁኔታ እንዲሸጥ እና እንዲያስተዋውቅ የሚያስችል ሲሆን፤ ደንበኞች በተመረጡ ሬስቶራንቶች በ’BeU Delivery’ በኩል ምግብ በሚያዙበት ወቅት ፔፕሲን በነፃ እንዲያገኙ ዕድል ይሰጣል።

ሁለቱ ተቋማት በጋራ በመሥራት የኢትዮጵያን የአገልግሎት ዘርፍ ለማዘመንና ተጨማሪ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ገልጸዋል።

ሞሐ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ፔፕሲ፣ ሚሪንዳ እና 7አፕ ምርቶችን ለደንበኞቹ እያቀረበ የሚገኝ ሲሆን ተቋሙ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕን ከተቀላቀለ በኋላ የነበሩበትን ችግሮች በመቅረፍ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል።

‘BeU Delivery’ ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ በኦንላይን የተለያዩ የምግብና የሸቀጣ ሸቀጥ ምርቶችን ለደንበኞች በማቅረብ ላይ ይገኛል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት