አቶ ጀማል ለምክር ቤቱ ከቀረቡ እጩዎች ውስጥ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያወጣውን መስፈርት በማሟላታቸው ነው ያሸነፉት።
የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በቅርቡ ባወጣው መመሪያ መሰረት የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ለመሆን አንድ ተወዳዳሪ የአንድ ቢሊዮን ብር ካፒታልና ሁለት ፋብሪካዎች ሊኖሩት እንደሚገባ መወሰኑ ይታወሳል።
አቶ ጀማል አህመድ ከ45 በላይ ኩባንያዎችንና ከ80 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያሉትን ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕን በብቃት እየመሩ የሚገኙ መሪ ናቸው።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በአግሮ ፣በማኑፋክቸሪንግ፣ በማእድን ፣በኮንስትራክሽንና ሪልስቴት፣ በንግድና ሆስፒታሊቲ ዘርፎች በመሰማራት ለሀገር ኢኮኖሚ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ የሚገኝ ተቋም ነው።
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የማኔጅመንት አባላትና መላው ሰራተኛ አቶ ጀማል አህመድ ፕሬዚዳንት ሆነው በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ እየገለጹ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆን ተመኝተዋል።
አገር አቀፉ የዘርፍ ምክር ቤት ከአቶ ጀማል በተጨማሪ አቶ በላይነህ ክንዴን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት
ኤፕሪ 7 2026
አጠቃላይየሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ የኢትዮጵያ አገር አቀፍ የዘርፍ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ።
አቶ ጀማል ለምክር ቤቱ ከቀረቡ እጩዎች ውስጥ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ያወጣውን መስፈርት በማሟላታቸው ነው ያሸነፉት።የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በቅርቡ ባወጣው መመሪያ መሰረት የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ለመሆን አንድ ተወዳዳሪ የአንድ ቢሊዮን ብር ካፒታልና ሁለት ፋብሪካዎች ሊኖሩት እንደሚገባ መወሰኑ ይታወሳል።አቶ ጀማል አህመድ ከ45 በላይ ኩባንያዎችንና ከ80 ሺህ በላይ ሰራተኞች ያሉትን ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕን በብቃት እየመሩ የሚገኙ መሪ ናቸው።ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ […]

