ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
ኤፕሪ 23 2026
አጠቃላይ

ዳሸን ባንክ የተመሰረተበትን 30ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በተከፈተው የዳሸን ኤክስፖ ላይ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የተለያዩ ምርቶችንና አገልግሎቶቹን በመያዝ እየተሳተፈ ነው።

‎ኤክስፖውን የዳሽን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበር አቶ ዱላ መኮንን፣ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አስፋው አለሙና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ በይፋ ከፍተዋል። ‎በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር የሚገኙ ድርጅቶችም ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ይዘው በኤክስፖው ላይ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 9 ቀናት የሚቆዩ ይሆናል። ‎የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ፤ ለመላው የዳሸን ባንክ […]

photo 2026 04 23 21 39 38
photo 2026 04 23 21 39 38

‎ኤክስፖውን የዳሽን ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀ-መንበር አቶ ዱላ መኮንን፣ የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አስፋው አለሙና የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ በይፋ ከፍተዋል።

‎በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ስር የሚገኙ ድርጅቶችም ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ይዘው በኤክስፖው ላይ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 9 ቀናት የሚቆዩ ይሆናል።

‎የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ፤ ለመላው የዳሸን ባንክ አመራሮች፣ ሰራተኞችና ባለአክሲዮኖች እንኳን ለ30ኛው ዓመት የምስረታ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

‎ባንኩ ባለፉት 30 ዓመታት አዳዲስና ዘመናዊ አሰራሮችን ለኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ በማስተዋወቅ ለዘርፉ እድገት ትልቅ አሻራ ማሳረፍ ችሏል።

‎የዳሸን ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አስፋው አለሙ፤ በክቡር ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አሊ አል-አሙዲ ሃሳብ አመንጪነት ከ30 ዓመታት በፊት ስራ የጀመረው ዳሸን ባንክ፣ ከኢትዮጵያ የግል ባንኮች ፈር ቀዳጅ በመሆን ለደንበኞቹ ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

‎ባንኩ በእነዚህ ዓመታት ዘርፉን ከማዘመን ባሻገር፣ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ ከሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋር በመቀናጀት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ነው።

‎ከሚያዝያ 15 እስከ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በየቀኑ ከረፋድ 4፡00 እስከ 10:00 ሰዓት በዳሸን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት የባንኩን 30ኛ ዓመት አብረው እያከበሩ የሚድሮክ ምርትና አገልግሎቶችን ይጎብኙ።

‎ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት