ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
ሴፕቴ 18 2026
አጠቃላይ

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለሠራተኞቹ 1.2 ቢሊዮን ብር ቦነስ መሰጠቱን ገለፁ።

በሚድሮክ ቤተሰብ ቀን ፕሮግራም ላይ የተገኙት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ፣ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 700 ሠራተኞች ለእያንዳንዳቸው ከ100 እስከ 500 ሺህ ብር ስጦታ ተሰጥቷል። አቶ ጀማል “የደጉ ሰው ደግ ተቋም” ሲሉ የገለጹት ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ በ2018 በጀት ዓመት 1.2 ቢሊዮን ብር ለሠራተኞቹ ቦነስ የሰጠ ሲሆን፣ 8.5 ቢሊዮን ብር […]

photo 2026 09 18 09 44 32
photo 2026 09 18 09 44 32

በሚድሮክ ቤተሰብ ቀን ፕሮግራም ላይ የተገኙት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ፣ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 700 ሠራተኞች ለእያንዳንዳቸው ከ100 እስከ 500 ሺህ ብር ስጦታ ተሰጥቷል።

አቶ ጀማል “የደጉ ሰው ደግ ተቋም” ሲሉ የገለጹት ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ በ2018 በጀት ዓመት 1.2 ቢሊዮን ብር ለሠራተኞቹ ቦነስ የሰጠ ሲሆን፣ 8.5 ቢሊዮን ብር ደሞዝ መክፈሉንና 390 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬን ለሀገር ማስገኘቱን ገልጸዋል።

አቶ ጀማል ለ2019 በጀት ዓመት የሠራተኞችን መነሻ ደሞዝ ወደ 10 ሺህ ብር ከፍ በማድረግ፣ ለደሞዝ ጭማሪ ተጨማሪ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
“ከትርፋችን 10 በመቶ ከፍለናል፤ ሚድሮክ የሕዝብ ነው የምንለው በምክንያት ነው” ያሉት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፣ ሚድሮክ ቀደም ብለው የተጀመሩትንና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለሀገር የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ገልጸዋል።

ይህንን እውን ለማድረግ ደግሞ ሁላችንም የሚድሮክ ሠራተኞች አራቱን የተቋሙን እሴቶች መሠረት በማድረግ፣ ለሚሠራው እያንዳንዱ ሥራ በተሰጠን የኃላፊነት ልክና ደረጃ ተጠያቂነትን እያሰፈንን፣ ኃላፊነታችንን በልኩ እየተወጣን፣ ለምናከናውነው እያንዳንዱ ሥራ ግልጽነትን መርህ አድርገን፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሚድሮክ የእኛ፣ የልጆቻችን፣ የቤተሰባችንና የሀገራችን ሀብት በመሆኑ፣ በባለቤትነት ስሜት በጋራ መሥራት አለብን ብለዋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለሠራተኞቹ 1.2 ቢሊዮን ብር ቦነስ መሰጠቱን ገለፁ። | ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ