ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
ኤፕሪ 20 2026
አጠቃላይ

‎በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ታሪክ ውስጥ ፈር ቀዳጅ የሆነው ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ!

‎ላለፉት ዓመታት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በዘርፉ በማስተዋወቅ፣ በኢትዮጵያ የግንባታ ዕድገት ውስጥ ትልቅ ድርሻ ተወጥቷል፤ አሻራውንም አስቀምጧል!‎‎በመንገድ፣ በሕንጻ፣ በስታዲየም ግንባታ፣ በኮንክሪት ምርትና በአስፓልት ፕላንት እንዲሁም በአሸዋ ምርት ሥራዎች ላይ በመሳተፍ፣ በኢትዮጵያ የዘመናዊ ግንባታ ሂደት ውስጥ የቀዳሚነት ሚናን በመጫወት ላይ የሚገኝ ኩባንያ ነው።‎‎በኢትዮጵያ ውስጥ ከተገነቡት ግዙፍ ግንባታዎች ጀርባ ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ አለ። የተቀናጀ የአመራር ሥርዓትን ተግባራዊ በማድረግ አርአያ […]

photo 2026 04 20 09 07 59
photo 2026 04 20 09 07 59

‎ላለፉት ዓመታት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በዘርፉ በማስተዋወቅ፣ በኢትዮጵያ የግንባታ ዕድገት ውስጥ ትልቅ ድርሻ ተወጥቷል፤ አሻራውንም አስቀምጧል!
‎
‎በመንገድ፣ በሕንጻ፣ በስታዲየም ግንባታ፣ በኮንክሪት ምርትና በአስፓልት ፕላንት እንዲሁም በአሸዋ ምርት ሥራዎች ላይ በመሳተፍ፣ በኢትዮጵያ የዘመናዊ ግንባታ ሂደት ውስጥ የቀዳሚነት ሚናን በመጫወት ላይ የሚገኝ ኩባንያ ነው።
‎
‎በኢትዮጵያ ውስጥ ከተገነቡት ግዙፍ ግንባታዎች ጀርባ ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ አለ። የተቀናጀ የአመራር ሥርዓትን ተግባራዊ በማድረግ አርአያ የሆነው ሚድሮክ ኮንስትራክሽን፣ በአሁኑ ወቅትም ግዙፍ ግንባታዎችን እያከናወነ ይገኛል።
‎
‎የ15 ሕንጻዎችን፣ የአንድ መንገድ፣ የአንድ አውሮፕላን ማረፊያ፣ የሁለት ስታዲየሞችን እንዲሁም በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙ ስድስት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ግንባታ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ 24 ሰዓት እየተሰራ ነው።
‎
‎የሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ አመራሮችና ባልደረቦች ያለፉትን ስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸማቸውን በጋራ ገምግመዋል። የዘርፉ ባለሙያዎች ባለፉት ስምንት ወራት ያከናወኗቸውን ተግባራት በጥሩ ሁኔታ ገምግመው፣ በቀሪ ወራት ከዚህ በበለጠ ለመሥራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
‎
‎የሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወልዳይ በርሄ ለተገኘው ስኬት ባልደረቦቻቸውን አመስግነው፣ በቀጣይ ከዚህ በበለጠ በርትተው እንዲሠሩ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
‎
‎የኮንስትራክሽንና ሪል እስቴት ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚን ወክለው ንግግር ያደረጉት ኮንስትራክሽን ኦፕሬሽን ኮርፖሬት ዳይሬክተር ኢንጂነር ዛህራ አብዱልሃዲ ዘርፉ ለድርጅቱ ስኬት የሚያደርገዉን ድጋፍ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልፀዋል።
‎
‎ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት!