ሚድሮክ ሰባቱንም የቡና ምርቶቹን ይዞ ሕዳር 13 እና 14/2018 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው የቡና ፌስቲቫል ላይ እየተሳተፈ ነው ።
ተወደው የሚጠጡ የቡና ምርቶቹም በበቃ፣ ሊሙ፣ አየሁ፣ ገማድሮ፣ ዱየና፣ በሃ እና ሆራይዘን ናቸው።
በፌስቲቫሉ ላይ ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ ዜጎች በመገኘት የሚድሮክ የቡና ምርቶችን እያጣጣሙና እየጎበኙ ነው።
የቡና አምራች ኩባንያዎች የተለያዩ ዓይነት የቡና ምርቶቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን፤ ለኤክስፖርት የተዘጋጁ የቡና ምርቶችን ጨምሮ ለእይታ ቀርበዋል፡፡
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በቡና ዘርፍ በስድስት ሰፋፊ እርሻዎቹ ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን ያሟሉ ምርቶች በማዘጋጀት ወደ ዉጪ ሀገራት በመላክ ለሃገራችን የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት ላይ ይገኛል።
ቡናን ከማምረት በተጨማሪ የማዘጋጀትና የማከማቸት አገልግሎትም ይሰጣል። በምርትና አገልግሎቱም እንደ ሃገር በተደጋጋሚ ጊዜያት ተሸላሚ መሆኑ ይታወቃል።
ሚድሮክ ለሀገር- ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ





