ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
ጃን 21 2026
አጠቃላይ

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋቢ ሸበሌ ሆቴልን ገዛ።

ኢትዮጵያ  32ኛውን  የዓለም  የአየር ንብረት  ለውጥ ጉባኤ ለማዘጋጀት መመረጧን ተከትሎ ሚድሮክ  ለተሳታፊዎች  ከሚሰራቸው ሆቴሎች አንዱ ሲሆን ዘመናዊና ቅንጡ በሆነ መልኩ የማሪዮት ደረጃን (autograph collection by Marriot ) ጠብቆ የሚታደስ ይሆናል። ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድና የዋቢ ሸበሌ ሆቴል አክሲዮን ማህበር የቦርድ ፀሀፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን ተፈራርመዋል። አቶ ጀማል አሕመድ የሆቴሉን […]

photo 2026 01 21 14 35 28
photo 2026 01 21 14 35 28

ኢትዮጵያ  32ኛውን  የዓለም  የአየር ንብረት  ለውጥ ጉባኤ ለማዘጋጀት መመረጧን ተከትሎ ሚድሮክ  ለተሳታፊዎች  ከሚሰራቸው ሆቴሎች አንዱ ሲሆን ዘመናዊና ቅንጡ በሆነ መልኩ የማሪዮት ደረጃን (autograph collection by Marriot ) ጠብቆ የሚታደስ ይሆናል።

ስምምነቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድና የዋቢ ሸበሌ ሆቴል አክሲዮን ማህበር የቦርድ ፀሀፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን ተፈራርመዋል።

አቶ ጀማል አሕመድ የሆቴሉን አገልግሎት በዘርፉ አለም በደረሰበት ደረጃ በማዘመን ለእንግዶች ምቹና ጥራቱን የጠበቀ የማረፊያ ቦታ ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የዋቤ ሸበሌ ሆቴል የቦርድ ፀሀፊ ልዑል በዕደማርያም መኮንን የሆቴሉን ታሪክ ጠብቆ በማዘመን ለትዉልድ ለማሻገር በመስማማቱ ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሚድሮክ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በከፍተኛ ጥራት በመገንባት ሀገሪቱ ከዘርፉ የምታገኘውን ዉጤት በማሳደግ ላይ የሚገኝ የሀገር ሀብት የሆነ ተቋም ነው።

ባሳለፈነው  ሳምንት  በሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  የተገነባው  ደንቢ ኤኮ ሎጅ ተመርቆ ወደ ስራ  መግባቱ  ይታወሳል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋቢ ሸበሌ ሆቴልን ገዛ። | ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ