በሚድሮክ ቤተሰብ ቀን ፕሮግራም ላይ የተገኙት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ፣ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 700 ሠራተኞች ለእያንዳንዳቸው ከ100 እስከ 500 ሺህ ብር ስጦታ ተሰጥቷል።
አቶ ጀማል “የደጉ ሰው ደግ ተቋም” ሲሉ የገለጹት ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ፣ በ2018 በጀት ዓመት 1.2 ቢሊዮን ብር ለሠራተኞቹ ቦነስ የሰጠ ሲሆን፣ 8.5 ቢሊዮን ብር ደሞዝ መክፈሉንና 390 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የውጭ ምንዛሬን ለሀገር ማስገኘቱን ገልጸዋል።
አቶ ጀማል ለ2019 በጀት ዓመት የሠራተኞችን መነሻ ደሞዝ ወደ 10 ሺህ ብር ከፍ በማድረግ፣ ለደሞዝ ጭማሪ ተጨማሪ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
“ከትርፋችን 10 በመቶ ከፍለናል፤ ሚድሮክ የሕዝብ ነው የምንለው በምክንያት ነው” ያሉት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፣ ሚድሮክ ቀደም ብለው የተጀመሩትንና አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በማጠናቀቅ ለሀገር የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥል ገልጸዋል።
ይህንን እውን ለማድረግ ደግሞ ሁላችንም የሚድሮክ ሠራተኞች አራቱን የተቋሙን እሴቶች መሠረት በማድረግ፣ ለሚሠራው እያንዳንዱ ሥራ በተሰጠን የኃላፊነት ልክና ደረጃ ተጠያቂነትን እያሰፈንን፣ ኃላፊነታችንን በልኩ እየተወጣን፣ ለምናከናውነው እያንዳንዱ ሥራ ግልጽነትን መርህ አድርገን፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሚድሮክ የእኛ፣ የልጆቻችን፣ የቤተሰባችንና የሀገራችን ሀብት በመሆኑ፣ በባለቤትነት ስሜት በጋራ መሥራት አለብን ብለዋል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት








