ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
ፌብ 5 2026
አጠቃላይ

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ዓለም አቀፍ የሲያናይድ ማኔጅመንት ሰርተፊኬት ማግኘቱ ለኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ትልቅ ትርጉም አለዉ። ሀብታሙ ተገኘ (ኢ/ር) የማዕድን ሚኒስትር

ዓለም አቀፍ የሲያናይድ ማኔጅመንት ጉባዔ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ኤሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል እየተካሄደ ሲሆን እስከ ነገ የሚቀጥል ይሆናል። በጉባኤዉ ላይ የተገኙት የማዕድን ሚንስትር ሀብታሙ ተገኘ (ኢ/ር ) ሚድሮክ ያገኘው በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን ዓለም አቀፍ የሲያናይድ ማኔጅመንት ሰርተፊኬት ለኢትዮጵያ ማዕድን ዘርፍ ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል። ይህም ኢትዮጵያ ከማዕድን ዘርፍ የምታገኘውን ዉጤት ከማሳደግ አንፃር ትልቅ ሚና ያለዉ […]

701A9955
701A9955

ዓለም አቀፍ የሲያናይድ ማኔጅመንት ጉባዔ በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ኤሌግዠሪ ኮሌክሽን ሆቴል እየተካሄደ ሲሆን እስከ ነገ የሚቀጥል ይሆናል።

በጉባኤዉ ላይ የተገኙት የማዕድን ሚንስትር ሀብታሙ ተገኘ (ኢ/ር ) ሚድሮክ ያገኘው በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን ዓለም አቀፍ የሲያናይድ ማኔጅመንት ሰርተፊኬት ለኢትዮጵያ ማዕድን ዘርፍ ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል።

ይህም ኢትዮጵያ ከማዕድን ዘርፍ የምታገኘውን ዉጤት ከማሳደግ አንፃር ትልቅ ሚና ያለዉ መሆኑን ገልፀው ለሌሎች በወርቅ ማዕድን ላይ ለተሰማሩ ተቋማት ምሳሌ ሊሆን የሚችል መሆኑን ጠቁመዋል።

ምርትን መጨመርና አከባቢ ጥበቃ ላይ ትልቅ ሚና ስላለው ሁሉም ተቋማት ይህን አሰራር ተከትለው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል ።

የዓለም አቀፍ የሲያናይድ ማኔጅመንት ፕሬዚዳንት ፖል በትማን ጉባኤው በኢትዮጵያ የተካሄደው የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኩባንያው ባስመዘገበው ዉጤት መሆኑን ገልፀዋል።

በጉባኤው የዘርፉ ተዋናዮች ልምድ ልዉዉጥ የሚያደርጉበት መድረክ መሆኑንም አንስተዋል።

ሚድሮክ ወርቅ በዕለቱ በሲያናይድ ትራንስፖርትና ማኔጅመንት ሲስተም እውቅና ተሰጥቶታል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – ሚድሮክ የሀገር

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ዓለም አቀፍ የሲያናይድ ማኔጅመንት ሰርተፊኬት ማግኘቱ ለኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ትልቅ ትርጉም አለዉ። ሀብታሙ ተገኘ (ኢ/ር) የማዕድን ሚኒስትር | ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ