ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
ፌብ 5 2026
አጠቃላይ

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ጉጂ ዞን ሻኪሶ ከተማ አውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ ነው።

አውሮፕላን ማረፊያ መሰረት ድንጋይ – ሚድሮክ ለሀገር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ጉጂ ዞን ሻኪሶ ከተማ አውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ ነው። የግንባታ መሰረተ ድንጋዩን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው አስቀምጠዋል፡፡ በመርሐ […]

photo 2026 02 05 14 23 05
photo 2026 02 05 14 23 05

አውሮፕላን ማረፊያ መሰረት ድንጋይ – ሚድሮክ ለሀገር

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ጉጂ ዞን ሻኪሶ ከተማ አውሮፕላን ማረፊያ ሊገነባ ነው።

የግንባታ መሰረተ ድንጋዩን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው አስቀምጠዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት፣ አባ ገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባሰለፈነዉ 2017 ዓ.ም በሻኪሶ ከተማ ያስገነባዉ የሚድሮክ ወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለማህበረሰቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

ሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃ/የተ/የግ/ማ ለሻኪሶ ከተማና ለአከባቢው ማህበረሰብ መንገድ በመሰራት፣ የመጠጥ ዉሃ በማስገባት፣ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት እና ሌሎች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል።

አሁንም ሚድሮክ የከተማዋን እድገት ለማፋጠንና የአከባቢውን ማህበረሰብ የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ለማስጀመር የመሰረት ድንጋይ በማስቀመጡ ደስታ ይሰማዋል።

የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታው መስከረም 2019 ዓ.ም የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት