ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
ዲሴም 21 2025
አጠቃላይ

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የቡና መቀሸሪያ ማሽኖችን ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ቤንች ሸኮና ሸካ ዞኖች አበረከተ።

ማሽኖቹ የቡና አምራቾች ምርታቸውን በጥራት እንዲያመርቱ ያስችላቸዋል። የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ ቡና አምራች አርሶአደሮች ማሽኖቹን በመጠቀም ቡናን ፈልፍሎ እሴት በመጨመር የበለጠ ዉጤታማ እንዲሆኑ የሚያደርገውን ድጋፍ ሚድሮክ አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት። ተቋሙ መሰል የማህበራዊ ኃላፊነት ስራዎች ላይ በመሳተፍ የህዝብ ሀብት መሆኑንን በተግባር እያረጋገጠ መሆኑንም ተናግረዋል ። ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የኢትዮጵያን የቡና […]

vlcsnap 2025 12 20 15h33m23s429
vlcsnap 2025 12 20 15h33m23s429

ማሽኖቹ የቡና አምራቾች ምርታቸውን በጥራት እንዲያመርቱ ያስችላቸዋል።

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ ቡና አምራች አርሶአደሮች ማሽኖቹን በመጠቀም ቡናን ፈልፍሎ እሴት በመጨመር የበለጠ ዉጤታማ እንዲሆኑ የሚያደርገውን ድጋፍ ሚድሮክ አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።

ተቋሙ መሰል የማህበራዊ ኃላፊነት ስራዎች ላይ በመሳተፍ የህዝብ ሀብት መሆኑንን በተግባር እያረጋገጠ መሆኑንም ተናግረዋል ።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የኢትዮጵያን የቡና ምርት ጥራትን በማሳደግ በአለም ገበያ ተፈላጊነቱን ከፍ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የግብርና ቢሮ ሃላፊ ዮሐንስ መላኩ ማሽኖቹ በምርት ሂደት የሚያጋጥሙ የምርት ብክነትን በመቀነስ አርሶአደሩ የልፋቱን ዉጤት እንዲያገኙ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

ሚድሮክ በተለያዩ ዘርፎች ለሀገር እድገት ከሚያደርገው አስተዋፅኦ በተጨማሪ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚሰራቸውን ስራዎች በማድነቅ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ተመሳሳይ የቡና መቀሸሪያ ማሽኖችን ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ማበርከቱ ይታወሳል።

ሚድሮክ ለሀገር – ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ