ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በአጠቃላይ 3 ሽልማቶችን አግኝቷል።
ሽልማቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አህመድ ከኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እጅ ተቀብለዋል።
በሳይንስ ሙዚየም “ፈጠራና እና ፍጥነት ለቡናችን ስኬት” በሚል መሪ-ቃል በተዘጋጀው ሀገር አቀፍ የቡና ኤግዚቢሽንና እዉቅና መርሐ ግብር ላይ ነው ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሽልማቱ የተሰጠው።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በጥራታቸውና በጣእማቸው ልዩ የሆኑ የተለያዩ የቡና ምርቶችን በማምረት ለውጭ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሬ እያስገኘ ያለ ተቋም ነው።
በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ የቡናና የሻይ ቅጠል እርሻዎቹ ለአካባቢው ማህበረሰብ ተጨማሪ የስራ እድል በመፍጠር ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል።
ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ከአመታዊ ትርፉ አስር በመቶውን ለማህበራዊ ሃላፊነት በመመደብ ሀገራዊ ግዴታውን እየተወጣ የሚገኝ የሀገር ሀብት ነው።
ሚድሮክ ለሀገር – ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ





