ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ
ማርች 30 2026
አጠቃላይ

‎ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለአንጋፋው ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግርኳስ ክለብ የ50ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለአንጋፋው ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግርኳስ ክለብ የ50ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።‎ድጋፉን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ ለክለቡ ተወካዮች የአዲስ አበባ መስተዳድር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት አስረክበዋል።‎‎ክለቡን ወደ ነበረበት ክብር ለመመለስ ሚድሮክ ዘላቂነት ያለዉን ድጋፍ እንደሚያደርግ የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚዉ ሁሉም የክለቡ ደጋፊዎችና ስለ ክለቡ ያገባኛል የሚሉ አካላት በባለቤትነት ስሜት መንቀሳቀስ […]

WhatsApp Image 2026 03 30 at 10.08.551
WhatsApp Image 2026 03 30 at 10.08.551

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ለአንጋፋው ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግርኳስ ክለብ የ50ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።
‎ድጋፉን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ጀማል አሕመድ ለክለቡ ተወካዮች የአዲስ አበባ መስተዳድር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት አስረክበዋል።
‎
‎ክለቡን ወደ ነበረበት ክብር ለመመለስ ሚድሮክ ዘላቂነት ያለዉን ድጋፍ እንደሚያደርግ የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚዉ ሁሉም የክለቡ ደጋፊዎችና ስለ ክለቡ ያገባኛል የሚሉ አካላት በባለቤትነት ስሜት መንቀሳቀስ አለባቸው ብለዋል።
ኢትዮጵያ የእግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ገናና ስም ያለውና በ1928 ዓም የተመሰረተው በያዝነው ዓመት 90 ዓመት የሞላው ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብን ወደ ቀደመ ዝናው ለመመለስ ሚድሮክ የበኩሉን ድርሻ ይወጣል ብለዋል አቶ ጀማል አሕመድ።
‎
‎ሚድሮክ መሰል ድጋፎችን በማድረግ የተቋማትን ዘላቂነት ለማረጋገጥና የግለሰቦችን ሕይዎት በመታደግ የሚታወቅ ተቋም ነው።
‎
‎ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ – የሀገር ሀብት