ማኑፋክቸሪንግ · የተቋቋመው 1948
Addis Gas and Plastics Factory PLC
ቀድሞ Addis Gas and Box Factory (SEIE) በመባል የሚታወቀው Addis Gas and Plastic Factory PLC በ1948 ተመሠረተ።

አዲስ ጋዝና ፕላስቲክ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ። Addis Gas and Plastic Factory PLC ቀደም ሲል አዲስ ጋዝና ሣጥን ፋብሪካ Society Electro Industrial Ethiopia (SEIE) በመባል የሚታወቅ ሲሆን በ1948 በአንድ ኢትዮጵያዊና በሦስት የውጭ ዜጎች ተቋቁሟል። የኩባንያው የታሪክ መዛግብት እንደሚያሳዩት የካርቦን ዳይኦክሳይድ (Co2) ጋዝና የባትሪ ውሃ ያመርት የነበረ ሲሆን በ1967 በመንግሥት ተወርሷል። ከሰኔ 1997 ጀምሮ በቀድሞው ሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕና በአሁኑ MIDROC Investment Group ሥር ይገኛል። አዲስ ጋዝና ፕላስቲክ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ተጨማሪ ልዩ ልዩ ማሽኖችን በመትከል የማምረት አቅሙንና የሚያመርታቸውን ምርቶችና አገልግሎቶች ዓይነት በማስፋት ላይ ሲሆን የተለያዩ


